ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቁ የምስራቅ አፍሪካ ጂኦ ፖለቲካን ቀይሯል – ከንቲባ ከድር ጁሃር
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር “የጉባ ብስራቶች ፤ የመደመር መንግሥት ትሩፋቶች” በሚል መሪ ሃሳብ ሕዝባዊ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።
በውይይት መድረኩ ላይ ከንቲባ ከድር ጁሃር፣ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
ከንቲባ ከድር ጁሃር በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ መንግሥት ከሕዝብ ጋር በመሆን ከውጭና ከውስጥ የሚነሱ ጠላቶችን በመመከት አይቻልም የተባለውን የሕዳሴ ግድብ በማጠናቀቅ የምስራቅ አፍሪካ ጅኦ ፖለቲካ እንዲቀየር አድርጓል።
በአስተዳደሩ የለውጡ መንግሥት ከመጣ በኋላ በሴፍቲኔት፣ በሌማት ትሩፋት እንዲሁም በኢንዱስትሪ ልማት ትሩፋቶች ላይ በርካታ ስራዎች እንደተሰራ ተናግረዋል።
ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ የድሬዳዋ ወጣቶች በሌሊት ታክሲ ማሕበር ተደራጅተው “ለሊቱ የኛ ነው” በሚል ማህበረሰቡን በፍፁም ሥነ ምግባር እያገለገሉ እንደሚገኙ መመልከታቸውን ገልጸው÷ ይህም ለሌሎች አካባቢዎች በተሞክሮነት ሊወሰድ የሚገባ መሆኑን አንስተዋል።
በውይይት መድረኩ የተሳተፉ የሕብረተሰብ ክፍሎች የሕዳሴው ግድብ በተመረቀበት ወቅት የተበሰሩት የጉባ ብስራቶች የኢትዮጵያን መጻኢ ተስፋ ብሩህና ወደ ብልጽግና የሚያመራ መሆኑን የተረዳንበት ነው ብለዋል።
ለእነዚህ ታላላቅ የልማት ስራዎችም ድጋፋቸውን እንደሚያጠናክሩ አመልክተዋል።
በምንያህል መለሰ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!