ሊቨርፑል እና ቼልሲ ድል ቀናቸው
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ16ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሊቨርፑል እና ቼልሲ ተጋጣሚዎቻቸውን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።
ምሽት 12 ሰዓት በሊጉ ደካማ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው ሊቨርፑል ብራይተንን ባስተናገደበት ጨዋታ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
የሊቨርፑል ማሸነፊያ ግቦችን ሁጎ ኤኪቲኬ ገና ጨዋታው እንደተጀመረ በመጀመሪያው ደቂቃና በሁለተኛው አጋማሽ ከመረብ ጋር ማገናኘት ችሏል።
በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገው የቼልሲ እና ኤቨርተን ጨዋታ በቼልሲ የ2 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
የቼልሲን ማሸነፊያ ግቦች ኮል ፓልመር እና ማሎ ጉስቶ አስቆጥረዋል።
የሊጉ ጨዋታዎች ቀጥለው ሲደረጉ ምሽት 2 ሰዓት ከ30 በርንሌይ ከፉልሃም እንዲሁም አርሰናል ከወልቭስ ምሽት 5 ሰዓት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
በዮናስ ጌትነት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook WMCC
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!