Fana: At a Speed of Life!

በሁሉም ዘርፎች ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚያግዙ ተግባራት እየተከናወኑ ነው – አቶ ጥላሁን ከበደ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በሁሉም ዘርፎች ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚያግዙ ተግባራት እየተከናወኑ ነው አሉ፡፡

“የጉባ ብስራቶች፤ የመደመር መንግሥት ትሩፋቶች” በሚል መሪ ሃሳብ በዛሬው ዕለት በጅግጅጋ ከተማ ህዝባዊ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በውይይት መድረኩ ላይ እንዳሉት፥ የመደመር መንግሥት በሁሉም አካባቢዎች ያሉትን አቅሞች ለይቶ በማልማት ለህዝቡ ተጠቃሚነት እየተጋ ይገኛል፡፡

በለውጡ ዓመታት በተሰራው ስራ ስንዴ ከውጭ ማስገባት ማቆም መቻሉን አንስተው፥ በሁሉም ዘርፎች ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚያግዙ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ብለዋል።

የሶማሌ ክልል እምቅ የተፈጥሮ ሃብት ያለው ክልል በመሆኑ መንግስት ለአካባቢው ሁለንተናዊ ልማት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም አስረድተዋል።

በጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር ከህዝቡ የተነሱ የውሃ፣ የውስጥ ለውስጥ መንገድና ሌሎች የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ይደረጋል ነው ያሉት፡፡

የከተማዋ ነዋሪዎች በበኩላቸው በክልሉ ከለውጡ ወዲህ ባለፉት ዓመታት በርካታ የልማት ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልጸው፥ እነዚህ የልማት ሥራዎች መንግስትን የሚያስመሰግኑ ናቸው ብለዋል፡፡

መንግስት በክልሉና በከተማዋ ላከናወናቸው በርካታ የልማት ሥራዎች ህዝቡ ሰላሙን ከመጠበቅ ጀምሮ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ያነሱት የውይይቱ ተሳታፊዎች፥ ይህን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡

በጅግጅጋ ከተማ በግንባታ ላይ የሚገኘው መንገድ በፍጥነት እንዲጠናቀቅና ከዚህ በፊት ተጠይቀው ምላሽ ያላገኙ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ጠይቀዋል፡፡

መንግሥት በተለይም ለሥራ ፈጠራ የሰጠው ትኩረት የበለጠ ሊጠናከር ይገባል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.