Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ 5ኛውን የአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታ እንድታዘጋጅ ተመረጠች

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ‎ኢትዮጵያ 5ኛውን የአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታ እንድታዘጋጅ ተመርጣለች፡፡

‎4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታ እየተደረገ በሚገኝባት አንጎላ ሉዋንዳ ከተማ በተደረገ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ ውድድሩን የማዘጋጀት ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡

‎የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ኢትዮጵያ 5ኛውን የወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታ በማዘጋጀት ዙሪያ ለጠቅላላ ጉባኤው ንግግር አድርገዋል።

‎ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸውም የኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕዝብ ይህንን ትልቅ አሕጉራዊ ውድድር ለማዘጋጀት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው አብራርተዋል፡፡

‎በጥያቄው መሠረትም ጠቅላላ ጉባኤው የኢትዮጵያን የማዘጋጀት ጥያቄ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።

በሙባረክ ፋንታው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.