ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የገቢና ወጪ ምርቶች ትራንስፖርትን ይበልጥ ለማቀላጠፍ…
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የገቢና ወጪ ምርቶች ትራንስፖርትን ይበልጥ የተቀላጠፈ ለማድረግና ዘርፈ ብዙ ትስስራቸውን አጠናክሮ ለማስቀጠል ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ከጅቡቲ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር አብዱልቃድር ሁሴን ጋር ተወያይቷል፡፡
ሁለቱ ወገኖች በውይይታቸው በሀገራቱ መካከል ያለውን አጋርነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
የገቢና ወጪ ምርቶች ትራንስፖርትን ይበልጥ የተቀላጠፈ ለማድረግና የሁለቱን ሀገራት ዘርፈ ብዙ ትስስሮች አጠናክሮ ለማስቀጠል ቁርጠኛ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል፡፡
በአቶ አደም ፋራህ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በጅቡቲ የሥራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!