Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በወርልድ ቴኳንዶ ወንዶች የወርቅ ሜዳልያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ‎አብረሃም አዱኛ በወርልድ ቴኳንዶ ወንዶች 51 ኪሎ ግራም ውድድር ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳልያ አስገኝቷል፡፡

በአንጎላ ሉዋንዳ እየተደረገ በሚገኘው 4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታ አብረሃም አዱኛ ግብፃዊውን ማዚን አህመድን 2-0 በማሸነፍ ነው የወርቅ ሜዳልያ ያሸነፈው።

በተመሳሳይ በዛሬው ዕለት በተደረጉ ውድድሮች በሴቶች ሦስት የነሐስ ሜዳልያዎች የተገኙ ሲሆን፥ በ68 ኪሎ ግራም ወንዶች አብረሃም በቀለ ለሀገሩ ተጨማሪ የነሐስ ሜዳልያ አስገኝቷል፡፡

ነገም ውድድሮች ቀጥለው ሲደረጉ በወርልድ ቴኳንዶ በወንዶችም በሴቶችም ኢትዮጵያ በ6 ውድድሮች ትካፈላለች።

በሙባረክ ፋንታው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.