አማራ ባንክና ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ በሰነደ ሙዓለ ንዋይ ምዝገባ ላይ በትብብር ለመስራት ተስማሙ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አማራ ባንክ እና ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ በሰነደ ሙዓለ ንዋይ ምዝገባ ላይ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል።
የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዮሐንስ አያሌው (ዶ/ር) በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ወቅት እንዳሉት÷ ዘመናዊና የተማከለ የካፒታል ገበያ መቋቋሙ ተጨማሪ እድሎችን ለመጠቀምና በዘርፉ ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ እድል ፈጥሯል።
በስምምነቱ መሰረት አማራ ባንክ በባለአክሲዮኖቹ የተያዙ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን የማዘጋጀት፣ ማስተባበርና ከካፒታል ገበያ ጋር የተያያዙ የማማከር ስራ ሃላፊነቶችን ለወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ መስጠቱን ተናግረዋል፡፡
በዚህም በሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ላይ የባንኩን አክሲዮኖች እንዲሸጥ ለማስቻል፣ የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪ ተቋም ለማቋቋም፣ ተጨማሪ ካፒታል ማሰባሰብና ሌሎች ተግባራትን አጠናክሮ ለማስቀጠል ስምምነቱ ወሳኝ ርምጃ ነው ብለዋል።
እንዲሁም አዳዲስ እና ደንበኛን ያማከለ የፋይናንስ አገልግሎት መስጠት እንደሚያግዝ ጠቅሰው ÷ ባንኩ የፋይናንስ አካታችነትን ለማጎልበትና ለባለ አክሲዮኖች፣ ለደንበኞቹና ለመላው ሕብረተሰብ ዘላቂ እሴት ለመፍጠር ያስችላል ነው ያሉት።
የወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክታዊት ዳዊት በበኩላቸው÷ባንኩ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ የፋይናንስ ዘርፉን ለመደገፍ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ከሚሰሩ ኩባንያዎች ጋር በትብብር እየሰራ ነው ብለዋል፡፡
አማራ ባንክ በሀገሪቱ የካፒታል ገበያ ውስጥ ለሚኖረው ሚናና ተሳትፎ በወጋገን ካፒታል ላይ ለጣለው ኃላፊነት አመስግነው ÷ በኢትዮጵያ የፋይናንስና ገበያዎች ልማት ውስጥ ያለውን ሚና ለማጠናከር እንደሚሰራ ጠቁመዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!