ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አርባ ምንጭ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ10ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አርባ ምንጭ ከተማን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
ቀን 9 ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የማሸነፊያ ግቦች አዲስ ግደይ (2) እና ሳይመን ፒተር አስቆጥረዋል፡፡
አርባምንጭ ከተማን ከሽንፈት ያልታደግችውን ብቸኛ ግብ ቡታቃ ሸመና ከመረብ አሳርፏል፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ ምድረገነት ሽረ ከባህር ዳር ከተማ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡
የሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል ምሽት 12:00 መቐለ 70 እንደርታ ከሀድያ ሆሳዕና በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይገናኛሉ፡፡