በጅግጅጋ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሥራ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተመርቆ በዛሬው ዕለት ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል።
አገልግሎቱን የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ እና በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴዔታ አክሊሉ ታደሰ አስጀምረውታል።
በጅግጅጋ ከተማ የተገነባው ማዕከሉ በመጀመሪያ ምዕራፍ በ9 ተቋማት 32 አገልግሎቶችን አቀናጅቶ የሚሰጥ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ዜጎች በቴክኖሎጂ በመታገዝ በአንድ ቦታ በርካታ አገልግሎቶችን የሚያገኙበት ዘመናዊ አሰራር ነው፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!