Fana: At a Speed of Life!

የዕለቱ የሊጉ ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ10ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዛሬ ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ።

ቀን 10 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የተደረገው የሲዳማ ቡና እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡

ለሲዳማ ቡና ፍፁም ጥላሁን (በራስ ላይ) ሲያስቆጥር ሀብታሙ ጉልላት የፈረሰኞቹን የአቻነት ግብ አስቆጥሯል፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም የተካሄደው የመቻል እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጨዋታ ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡

ቀን 7:00 ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም የተካሄደው ጨዋታ የድሬዳዋ ከተማ እና አዳማ ከተማ 1 ለ 1 በሆነ ውጤት መጠናቀቁ ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.