የአሜሪካ እና ሩሲያ ባለስልጣናት በሩሲያ ዩክሬን ሰላም ዙሪያ የሚያደርጉት ውይይት ቀጥሏል
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሩሲያ እና ዩክሬን ወደ ሰላም እንዲመጡ ለማድረግ ያለመው የአሜሪካ እና ሩሲያ ልዩ መልዕክተኞች ውይይት በአሜሪካ ሚያሚ እየተካሄደ ነው፡፡
ውይይቱ የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የሩሲያና ዩክሬን ጦርነትን በሰላም ድርድር ለመቋጨት የሚያደርገው ጥረት አካል ነው ተብሏል፡፡
ውይይቱን አስመልክተው ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የክሬምሊን ልዩ መልዕክተኛ ኪሪል ዲሜትሪቭ÷ ለሁለት ቀናት በሚያሚ እየተካሄደ የሚገኘውን ውይይት “ገንቢ” ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ውይይቱ የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት በሰላም ድርድር እንዲቋጭ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ባቀረቧቸው 20 የድርድር ነጥቦች ላይ ያተኮረ መሆኑን መናገራቸውን መወያየታቸውን የሩሲያ መገናኛ ብዙሀኖች ዘግበዋል፡፡
ዛሬ ቀጥሎ እየተካሄደ በሚገኘው የአሜሪካ እና ሩሲያ ልዩ መልዕክተኞች የሰላም ውይይት ወደ ስምምነት የሚያመራ ከሆነ የሩሲያ እና ዩክሬን ተደራዳሪዎች ፊት ለፊት ተገናኝተው እንደሚነጋገሩ ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡
የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ እንዳሉት፤ አሜሪካ ባቀረበችው የሰላም ሀሳብ መሰረት ሩሲያና ዩክሬን በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ የፊት ለፊት ውይይታቸውን ሊያደርጉ ይችላሉ።
በሚኪያስ አየለ