ምርጫ ቦርድ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዙሪያ ከፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር ተወያየ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዙሪያ ከፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር ተወያይቷል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ረቂቅ የጊዜ ሠሌዳ ጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
በዚህ ወቅትም “የዕጩዎች የድጋፍ ፊርማ ማቅረብ ይቅር/ይታገድ” እና “ከገዢው ፓርቲ ጋር መወያየት እንፈልጋለን” የሚሉ ጥያቄዎች ከፖለቲካ ፓርቲዎች ተነስተው እንደነበር ተጠቅሷል፡፡
ቦርዱም ከፓርቲዎች የተነሱ ጥያቄዎች መልስ ሊያገኙ በሚችሉበት አግባብ ላይ ሲሠራ መቆየቱ ነው የተገለጸው፡፡
በዚህ መሰረትም የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሕዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባው “የዕጩዎች የድጋፍ ፊርማ ማቅረብ” የሚለውን ሃሳብ ማገዱ ተመላክቷል፡፡
በዛሬው ዕለትም ምርጫ ቦርድ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ ገዢውን ፓርቲ ጨምሮ ከፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር መክሯል።
የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ በዚህ ወቅት ÷ መድረኩ የተዘጋጀው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሐዊና ገለልተኛ እንዲሆን ከማን ምን ይጠበቃል፣ አስቻይ የፖለቲካ ምኅዳር መፍጠርን እንዲሁም የውይይቱ ቀጣይነት በምን መልኩ መሆን አለበት የሚለውን የሁሉም ፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ባሉበት መወያየት አስፈላጊ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡
ተሣታፊ ፖለቲካ ፓርቲዎቹ የዕጩ ድጋፍ ፊርማ ማቅረብ መታገድን እና የመድረኩ መዘጋጀትን አስመልክቶ ለቦርዱ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል፡፡
ምርጫውን አስመልክቶ መሟላት አሉባቸው ያሏቸውን ሁነቶች አስቻይ ሁኔታና የውይይቱ ቀጣይነትን ጨምሮ በርካታ ጉዳዮች ላይ ተሣታፊ ፖለቲካ ፓርቲዎቹ ያሏቸውን አስተያየቶችና ጥያቄዎች አጋርተዋል።
ሰብሳቢዋ በማጠቃለያ ንግግራቸው የፀጥታ አስቻይ ሁኔታን በተመለከተና ሌሎች ምርጫውን የተመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ የሚኖሩ የምክክርና የውይይት መድረኮች ቀጣይነት እንዳላቸው ተናግረዋል።
የአስፈጻሚዎችን ገለልተኝነት አስመልክቶ ለተነሣው ጥያቄ ቦርዱ ዝርዝራቸውን ለፖለቲካ ፓርቲዎቹ መላኩን አመልክተዋል፡፡
በገለልተኝነቱ/ቷ ላይ ጥያቄ ያላቸው አስፈጻሚ ካገኙ ዝርዝሩን እንዲልኩ ቦርዱ በመጠበቅ ላይ መሆኑ ን አንስተው÷ በተመሳሳይ መልኩ ለፓርቲዎች በጀት ለማከፋፈልም ፓርቲዎቹ ሠነድ እንዲያቀርቡ እየተጠበቀ ነው ብለዋል፡፡
“በትግራይ ምርጫ ይካሄዳል ወይ” ለሚለው ጥያቄም ቦርዱ በሌሎች ክልሎች እንደሚያደርገው በትግራይ ክልልም ምርጫ ለማድረግ ዝግጅት እያከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡
ባሳለፍነው ሣምንትም ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር በትግራይ ምርጫ ስለሚካሄድበት ሁኔታ እንደተወያዩና ቦርዱ ምክክሩን ተከትሎ ጥሩ ውጤት እንደሚጠብቅ አብራርተዋል፡፡
![]()
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!