Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ ዋንጫ ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡

በዕለቱ የመጀመሪያ መርሐ ግብር በምድብ ሦስት የሚገኙት ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ቤኒን ቀን 9 ሰዓት ከ30 ይገናኛሉ፡፡

በዚሁ ምድብ የሚገኙት ሴኔጋል እና ቦትስዋና ምሽት 12 ሰዓት የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

በምድብ-4 ናይጄሪያ ከታንዛኒያ ምሽት 2 ሰዓት ከ30 እንዲሁም ቱኒዚያ ከዩጋንዳ ምሽት 5 ሰዓት የሚደረጉ የዛሬ ጨዋታዎች ናቸው፡፡

ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች ደቡብ አፍሪካ አንጎላን፣ ግብጽ ዚምባብዌን በተመሳሳይ 2 ለ 1 ሲያሸንፉ፥ ማሊ ከዛምቢያ 1 ለ 1 አቻ ተለያይተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.