ስለኢትዮጵያ የውይይት መድረክ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ስለኢትዮጵያ የውይይት መድረክ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መገኛ ጉባ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሃሰን፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ እና የተለያዩ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
አቶ አሻድሊ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ መድረኩ የኢትዮጵያ ብልጽግና አይቀሬነት ማረጋገጫ በሆነው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ላይ መካሄዱ ልዩ ያደርገዋል፡፡
የኢትዮጵያ የመልማት ፍላጎት ፍሬ ወደተለያዩ ዘርፎች እንዲደርስ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቅሰዋል።
ክልሉ ከራስ አልፎ ለሀገር መትረፍ የሚችልበትን እምቅ አቅም ከሕብረተሰቡ ጋር ለማስተሳሰር በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የተዘጋጀው የውይይት መድረኩ “ሕዳሴ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
በመድረኩ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በተለያዩ ዘርፎች የሚኖረውን አስተዋጽኦ የዳሰሱ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበዋል።
በአሸናፊ ሽብሩ