የኦሞ ባንክ አጠቃላይ የሃብት መጠን 9 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ደረሰ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኦሞ ባንክ አጠቃላይ የሀብት መጠኑ 9 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ደርሷል አሉ የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጥላሁን ከበደ፡፡
ኦሞ ባንክ አራተኛ መደበኛ እና ሶስተኛ አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔውን እያካሄደ ነው፡፡
አቶ ጥላሁን ከበደ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ባንኩ ከታክስ በፊት 213 ሚሊየን ብር ትርፍ አስመዝግቧል።
የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑም 6 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር መድረሱን ነው የገለጹት፡፡
ባንኩ ልማት ተኮር ርዕዩን ለማሳካት በግብርና፣ በንግድ እንዲሁም በአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ዘርፍ ለተሰማሩ ደንበኞች ብድር እያመቻቸ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
በዚህም የሀገር ውስጥ ኢኮኖሚን በመደገፍ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ጠቅሰው÷ የቅርንጫፎቹን ቁጥር ወደ 241 ማሳደጉን አመልክተዋል፡፡
በሐመልማል ዋለ