Fana: At a Speed of Life!

ግብጽ ደቡብ አፍሪካን አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ ዛሬ ቀጥሎ ሲካሄድ ግብጽ ደቡብ አፍሪካን 1 ለ 0 አሸንፋለች።

ምሽት 12 ሰዓት በተደረገው ጨዋታ ግብጽ መሐመድ ሳላህ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠራት ግብ ሶስት ነጥብ ይዛ ወጥታለች።

የግብጹ መሐመድ ሀኒ በሁለት ቢጫ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

ግብጽ ሁለቱንም የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች ማሸነፏን ተከትሎ በ6 ነጥቦች ወደጥሎ ማለፉ መግባቷን አረጋግጣለች።

ጨዋታው ቀጥሎ ሲካሄድ ምሽት 2 ሰዓት ከ30 በምድብ አንድ የሚገኙት ዛምቢያ ከኮሞሮስ እንዲሁም ምሽት 5 ሰዓት አዘጋጇ ሞሮኮ ከማሊ ጋር ይጫወታሉ።

ቀን 9 ሰዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ አንጎላ እና ዚምባቡዌ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት መለያየታቸው ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.