Fana: At a Speed of Life!

በቁልቢ የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል በድምቀት እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዓመታዊው የቅዱስ ገብርዔል የንግስ በዓል በቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በተለያዩ ሐይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች በድምቀት እየተከበረ ነው።
የሐይማኖት አባቶች፣ ዲያቆናት፣ የሰንበት ተማሪዎችና ምዕመናን በዓሉን በቅዳሴ፣ በዝማሬ፣ በፀሎትና በሌሎች ሐይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች እያከበሩ ይገኛሉ።
በንግስ በዓል አከባበሩ ላይ ከሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እንዲሁም ከውጭ የመጡ በርካታ ምዕመናን ተገኝተዋል።
በተመሳሳይ ዓመታዊ የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በርካታ ምዕመናን በተገኙበት በሀዋሳ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል፡፡
በዓሉን ለመታደም ወደ ከተማዋ ያቀኑትን በርካታ ምዕመናን የከተማው አስተዳደር እና ማሕበረሰቡ ድንኳን በመጣል ደማቅ አቀባበል አድርገዋል፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ ታሕሣሥ 19 የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በድምቀት ይከበራል።
በተስፋዬ ሃይሉ እና ብርሃኑ በጋሻው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook WMCC
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.