Fana: At a Speed of Life!

የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ የአፈር ለምነትን ለማሻሻል…

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የ2018 ዓ.ም የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ንቅናቄ መድረክ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ከሚሴ ከተማ አካሂዷል፡፡

በመርሐ ግብሩ በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፣ የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ ደረጀ ማንደፍሮ እና በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅ/ጽ/ቤት ሃላፊ ይርጋ ሲሳይ ተገኝተዋል፡፡

አቶ ደረጀ ማንደፍሮ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ የአፈር ለምነትን በማሻሻል የግብርና ዘርፉን ምርታማነት ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡

የብሔረሰብ አስተዳደሩ በክልሉ ትልቅ ተሞክሮ የሚወሰድበት አካባቢ መሆኑን ጠቁመው÷ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማትን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

የተፈጥሮ ሃብት ልማት ሥራ በክልሉ ያለውን የመሬት ሃብት በአግባቡ ተጠቅሞ ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ ጉልህ ሚና እንዳለው ተመላክቷል፡፡

በአማራ ክልል በ2018 ዓ.ም ከ456 ሺህ በላይ ሔክታር መሬት ላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ለማከናወን የታቀደ ሲሆን÷ በዚህም ከ4 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ዜጎች ይሳተፋሉ፡፡

የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ንቅናቄ ሥራ የሚከናወንባቸው 9 ሺህ 200 በላይ ተፋሰሶች መለየታቸውም ነው የተገለጸው፡፡

የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ለአፈር ለምነት ከፍተኛ ሚና ያለው በመሆኑ ማሕበረሰቡ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በከድር መሀመድ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.