Fana: At a Speed of Life!

የሀላባ ሕዝብ የጥንካሬና አንድነት ምልክት የሆነው ሴራ…

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀላባ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ በዓል ሴራ ‘‘የሴራ በዓላችን በሕብር የመቻላችን አቅም ማሳያ’’ በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ተከብሯል፡፡

በበዓሉ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሂክማ ከይረዲን የሴራ በዓል የሀላባ ብሔረሰብ የማንነቱ፣ የዓላማውና የማይናወጥ የጋራ ጥንካሬ ህያው ምስክር መሆኑን አውስተዋል፡፡

በዓሉ የዘመን መለወጫ ብቻ አይደለም፤ የሀላባ ሕዝብ የጥንካሬ፣ አንድነትና ብሩህ ተስፋ ምልክት ነው ብለዋል።

የሴራ በዓል የሕዝቡን ማንነትና እሴቶች ከትውልድ ወደ ትውልድ በማስተላለፍ ባህላዊ እሴቶችና ማሕበራዊ ትስስሮችን ለማጠናከር ከፍተኛ አበርክቶ እንዳለውም ጠቁመዋል፡፡

የሀላባ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ መሐመድ አሚን በበኩላቸው÷ የሀላባ ሴራ በዓል በውስጡ በርካታ ማሕበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች የሚስተናገዱበት የብሔረሰቡ መተዳደሪያ ህግ መሆኑን ተናግረዋል።

በበዓሉ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎችና በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የሀላባ ብሔረሰብ ተወላጆች የተገኙ ሲሆን÷ የበዓሉ ማጠቃለያም በሀላባ ዞን ጥር 3 ቀን 2018 ዓ.ም በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል፡፡

በሔኖክ ለሜ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.