የዲሜ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ ”ቤትኽ” በዓል እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዲሜ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ ”ቤትኽ” በዓል በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው፡፡
የሳላማጎ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ህጉ ቅጣቱ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት÷ ኢትዮጵያ በበርካታ ልዩነት ውስጥ አንድነቷን አስጠብቃ የቆየች ሀገር መሆኗን አውስተዋል፡፡
የዲሜ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ ”ቤትኽ” የመቻቻልና የአብሮነት በዓል መሆኑን ጠቅሰው ÷ በዓሉ ከሌሎች ወንድም የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጋር በጋራ እየተከበረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በወረዳው ያልተዳሰሱ በርካታ ቱባ ባህሎች መኖራቸውን የገለጹት ዋና አስተዳዳሪው ÷ እሴቶቹ ለጥናትና ምርምር እንዲሁም ለቱሪስት መዳረሻነት ክፍት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ በበኩላቸው ÷ በዓሉ የተጣላ የሚታረቅበትና አብሮነት የሚጠናከርበት እንዲሁም አባቶች ትውልዱን የሚመርቁበት ነው ብለዋል፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል አጉ ደባን ÷ የማሕበረሰቡን መልካም እሴቶች በጥናት በማስደገፍ ለዓለም ማሕበረሰብ ለማስተዋወቅ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
”ቤትኽ” የዲሜ ብሔረሰብ ካለፈው ስህተታቸው ተምረው ለተሻለ እድገት የሚሰናዱበት፣ ቂምና ጥላቻን የሚሽሩበትና ፈጣሪያቸውን የሚያመሰግኑበት በዓል መሆኑን የደቡብ ኦሞ ዞን ኮሙኒኬሽን ቢሮ ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!