Fana: At a Speed of Life!

ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ስኬት የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት…

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ስኬት የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነትን ለማስፋት እየተሰራ ነው አለ።

በሚኒስቴሩ የኤሌክትሪፊኬሽንና ኢነርጂ መረጃ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ዳባ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት፥ ባለፉት ሰባት ዓመታት በብሔራዊ ኤሌትክሪፊኬሽን ፕሮግራም ከ2 ሚሊየን በላይ አባወራዎች የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያገኙ ተደርጓል።

ለዲጂታል 2030 ስትራቴጂ ስኬት በቀጣይ ዓመታት ለ9 ሚሊየን አባወራዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ከብሔራዊ ግሪድ ርቀው ለሚገኙ አካባቢዎች በቤተሰብና በማህበረሰብ ደረጃ የሶላር ኢነርጂ ቴክኖሎጂ ተደራሽ የማድረግ ግብ መኖሩንም ተናግረዋል።

በዚህም በአንድ አካባቢ እስከ 100 አባወራዎች መገለገያ የሶላር ኢነርጂ የኃይል ማቅረብ ስራዎች ይተገበራሉ ነው ያሉት።

ይህም የኤሌክትሪክ ሀይል አሁን ካለበት 63 በመቶ ወደ 75 በመቶ ከፍ እንደሚያደርግና ለዲጂታል 2030 ስትራቴጂ ስኬት እንደሚያግዝ ስራ አስፈጻሚው አብራርተዋል።

በበላይ ተስፋዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.