Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የቡና ቱሪዝም መዳረሻ መሆኗን ለማሳየት ያለመው መርሐ ግብር…

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቱሪዝም ሚኒስቴር የቡና ቱሪዝምን በተመለከተ ለመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብር እያካሄደ ነው።

መርሐ ግብሩ ኢትዮጵያ የአረቢካ ቡና መገኛ መሆኗን በማጉላትና ቡና ከኢትዮጵያውያን ባህል ጋር ያለውን ጥልቅ ቁርኝት በማሳየት ሀገሪቱ በባህል እና ቱሪዝም ዘርፍ ያላትን ተመራጭነት ለማስተዋወቅ ያለመ ነው።

በቡና አምራች አካባቢዎች የሚደረገው ጉዞ ጋዜጠኞች ከቡና ለቀማና ዝግጅት ጋር በተያያዘ ተግባራዊ ክንውኖች ላይ በመሳተፍ ከቡና ቱሪዝም ጋር እንዲተዋወቁ እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡

መርሐ ግብሩ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀዳሚ ቡና ላኪ ሀገር ብቻ ሳትሆን ተመራጭ የቡና ቱሪዝም መዳረሻ እና የውብ ባህሎች ባለቤት መሆኗን ለማሳየት ያስችላል።

የጋዜጠኞች ቡድን በሲዳማ ክልል የፌሮ አና አካባቢው ገበሬዎች ሁለገብ መሰረታዊ ሕብረት ሥራ ማህበር የሚያለማውን ቡና እንዲሁም ገደብ ወረዳ ተገኝቶ የይርጋጨፌ ቡናን ከለቀማ ጀምሮ ያለውን ሒደት ተመልክቷል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወይኒቱ መልኩ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ቡና ከኢኮኖሚያዊ ጥቅሙ ባሻገር ከባህላችን ጋር በእጅጉ የተሳሰረ በመሆኑ ማህበራዊ መስተጋብርነቱን ለቱሪዝም መስሕብነት ልንጠቀምበት ይገባል።

የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ቡድን ጉብኝቱን በመቀጠል የጅማ እና ካፋ ዞኖች ቡና አምራች አካባቢዎች የሚጓዝ ሲሆን÷ የቱሪዝም ሚኒስቴር ዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች፣ የጉዞ ባለሙያዎች እንዲሁም የባህልና የምግብ ቱሪዝም ባለድርሻ አካላት ተመሳሳይ መርሐ ግብሮች ላይ በመሳተፍ ዘርፉን የማስተዋወቅ ስራ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በምንተስኖት ሙሉጌታ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.