ሲንቄ ኢንቨስትመንት ባንክ ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የስራ ፈቃድ አገኘ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሲንቄ ኢንቨስትመንት ባንክ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ዘርፍ የራሱን ሚና ለመጫወት ፈቃድ ተቀብሎ በይፋ ስራ ጀምሯል።
በስራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የኢንቨስትመንት ባንኩ ስራ አስፈፃሚ ግርማ ሙለታ እንዳሉት፤ ለባንኩ የተሰጠው ፈቃድ ታሪካዊ እና የፈጣን ዕድገቱ ውጤት ነው።
የባንኩን ኢንዱስትሪን ከተቀላቀለ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ የፋይናንስ አፈፃፀም፣ የካፒታል መጠን ዕድገት የተቋማዊ ጥንካሬ እና የአስተዳደር ብቃት በማስመዝገብ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያን መቀላቀል እንደቻለም ነው የተናገሩት።
ሲንቄ ኢንቨስትመንት ባንክ ከ480 ሚሊየን ብር በላይ ኢንቨስት አድርጓል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሐና ተህልቁ በበኩላቸው በዘርፉ ላይ ለመሰማራት ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩን ገልጸው፤ የውጭ ተቋማት ጭምር ለመቀላቀል ጥያቄ አቅርበዋል ብለዋል።
በዛሬው ዕለት ስራውን የጀመረው የኢንቨስትመንት ባንኩም የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣንን የተቀላቀለ አምስተኛው ባንክ እንደሆነም ተናግረዋል።
በሰማኸኝ ንጋቱ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!