Fana: At a Speed of Life!

 በሻይ ልማት የግሉ ዘርፍ እሴት በማከል ቢሳተፍ ሀገራችንን ተጠቃሚ ያደርጋታል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሻይ ልማት የግሉ ዘርፍ እሴት በማከል ቢሳተፍ ሀገራችንን ተጠቃሚ ያደርጋታል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የአረንጓዴ ዐሻራ አካል የሆነው የሻይ ልማት ኢኒሼቲቭ ተከላው በጥሩ ሁኔታ እየተከወነ ነው ብለዋል።

በመትከል የታየው መልካም ጅማሮ በአግሮ–ፕሮሰሲንግ ከተደገመ ሙሉ እንደሚሆን ገልጸው፤ የግሉ ዘርፍ እሴት በማከል ቢሳተፍ ከሀገር ውስጥ ፍጆታ በተጨማሪ በወጪ ንግድ ሀገራችንን ተጠቃሚ ያደርጋታል ነው ያሉት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.