የአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ትልቅ የዕውቀት ማዕከል ሆኖ እያገለገለ ይገኛል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ትልቅ የዕውቀት ማዕከል ሆኖ እያገለገለ ይገኛል አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤና የአብርሆት ቤተ መጻሕፍት የቦርድ ሰብሳቢ ቡዜና አልከድር እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት የአብርሆት ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት አሰጣጡን የሚያጎለብቱ የዲጂታል ሲስተሞችን አስጀምሯል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚህ ወቅት÷ የአብርሆት ቤተ መጻሕፍት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጭነት ተገንብቶ ለአገልግሎት መብቃቱን አስታውሰዋል።
ቤተ መጻሕፍቱ አገልግሎት መስጠት በጀመረ ማግስት በመዲናዋ ትልቅ የዕውቀት ማዕከል ሆኖ እያገለገለ እንደሚገኝ ገልጸው÷ በዕውቀትና ክህሎት የተካነ ትውልድ በማፍራት ለኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ መሰረት የሚጥል ስፍራ መሆኑንም አብራርተዋል።
አገልግሎት አሰጣጡን በአዳዲስ አሰራሮች በማላቅ ዕውቀትን ለሚሹ ሁሉ የንባብ ባህልን በማዳበር የዕውቀት ሽግግር ድልድይ በመሆን አገልግሎት እየሰጠ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
የአብርሆት ቤተ መጻሕፍት የዲጂታል ሥርዓቶችም የንባብ አገልግሎት አሰጣጥ በተሻለ ጥራትና አቅም የሚያልቁ መሆናቸውን አመላክተዋል።
የዲጂታል አገልግሎቶቹም የቤተ መጻሕፍቱን የተቀናጀ አስተዳደር በማሳለጥ ተመራማሪዎች የጥናትና ምርምር ስራዎቻቸውን ካሉበት ቦታ ሆነው በቀላሉ ማከናወን የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል።
በቀጣይም ዜጎች የአብርሆት ቤተ መጻሕፍትን በ24 ሰዓት አገልግሎት የፈጠረውን ምቹ የንባብ ምኅዳር ሊጠቀሙበት እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ዋና ዳይሬክተር ሙሉቀን ታሪኩ በበኩላቸው÷ ቤተ መጻሕፍቱ የዜጎችን የንባብ ፍላጎት በሚመጥን መልኩ የ24 ሰዓት አገልግሎት እየሰጠ እንደሆነ መናገራቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
በዛሬው ዕለት የተጀመሩት የዲጂታል ሲስተሞች የአብርሆት ቤተመጻሕፍት በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ አቅም የሚፈጥሩ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook WMCC
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!