Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ ዋንጫ ሁለት የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሁለት የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት ይደረጋሉ፡፡

ምሽት 1 ሰዓት ላይ ሴኔጋል ከሱዳን ጋር ይገናኛሉ።

በምድብ ጨዋታዎች ሴኔጋል ሁለቱን በማሸነፍ እና በአንድ ጨዋታ አቻ በመለያየት በሰባት ነጥብ ከምድቧ 1ኛ ደረጃን በመያዝ ጥሎ ማለፉን የተቀላቀለች ሲሆን፤ ሱዳን ደግሞ በምድብ ጨዋታ በሁለት ተሸንፋ በሶስት ነጥብ ምርጥ ሶስተኛ ሆና ጥሎ ማለፉን መቀላቀሏ ይታወሳል።

ጨዋታው ምሽት 5 ሰዓት ላይ ቀጥሎ ሲካሄድ ማሊ እና ቱኒዚያ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

በምድብ ጨዋታ ማሊ ያደረገቻቸውን ሶስቱንም ጨዋታዎች በአቻ ውጤት በመለያየት በሶስት ነጥብ 2ኛ ደረጃ በመያዝ ነው ጥሎ ማለፉን የተቀላቀለችው።

ቱኒዚያ ደግሞ በምድብ ጨዋታ አንድ በማሸነፍ፣ አንድ አቻ በመለያየት እና በአንድ ጨዋታ ደግሞ ተሸንፋ ከምድቧ 2ኛ ደረጃን በመያዝ ጥሎ ማለፉን መቀላቀሏ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.