አስቶንቪላ ኖቲንግሃም ፎረስትን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት መርሐ ግብር አስቶንቪላ ኖቲንግሃም ፎረስትን 3 ለ 1 አሸንፏል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ከ30 በተረደገው ጨዋታ ኦሌ ዋትኪንስ እና ጆን ማክ ጊን (ሁለት) ለአስቶን ቪላ ግቦቹን ሲያስቆጥሩ ሞርጋን ጊብስ ዋይት የኖቲንግሃም ፎረስትን ብቸኛ ግብ ከመረብ አገናኝቷል።
ውጤቱን ተክትሎም አስቶንቪላ ነጥቡን ወደ 42 ከፍ አድርጓል።