Fana: At a Speed of Life!

ወልቭስ ዌስትሃም ዩናይትድን በማሸነፍ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን አስመዘገበ  

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ወልቭስ ዌስትሃም ዩናይትድን 3 ለ 0 በማሸነፍ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን አስመዝግቧል።

ምሽት 12 ሰዓት ላይ በሜዳው ዌስትሃም ዩናይትድን ያስተናገደው ወልቭስ አሪያስ፣ ዋንግ ሂ-ቻን (በፍጹም ቅጣት ምት) እና ማኔ ባስቆጠሯቸው ግቦች ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።

ባለፈው ሳምንት ወደ ኦልድ ትራፎርድ አቅንቶ ከማንቼስተር ዩናይትድ ጋር ነጥብ ተጋርቶ የተመለሰው ወልቭስ ዛሬ ባደረገው ጨዋታ በውድድር ዘመኑ በሊጉ ለመጀመሪያ ጊዜ ለማሸነፍ በቅቷል።

በሊጉ ግርጌ ላይ የሚገኘው ወልቭስ ነጥቡን 6 አድርሷል።

በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገ ጨዋታ ብራይተን በርንሌይን 2 ለ 0 አሸንፏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.