Fana: At a Speed of Life!

ማንቼስተር ሲቲ ከቼልሲ – ተጠባቂው ጨዋታ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ20ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ በሜዳው ኢትሃድ ምሽት 2 ሰዓት 30 ላይ ቼልሲን ያስተናግዳል።

በሊጉ ከተከታታይ ስድስት ጨዋታዎች ድል በኋላ ከሰንደርላንድ ጋር አቻ የተለያየው ማንቼስተር ሲቲ ከመሪው አርሰናል ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማጥበብ ይፋለማል፡፡

አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካን ያሰናበተው ቼልሲ በሊጉ ያለፉትን ሦስት ተከታታይ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም፡፡

ሁለቱ ቡድኖች በፕረሚየር ሊጉ እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ማንቼስተር ሲቲ አራቱን በማሸነፍ የበላይነት ያለው ሲሆን በአንዱ አቻ ተለያይተዋል፡፡

በዕለቱ የመጀመሪያ መርሐ ግብር ቀን 9 ሰዓት 30 ላይ ሊድስ ዩናይትድ ማንቼስተር ዩናይትድን ያስተናግዳል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ማንቼስተር ዩናይትድ በሦስቱ ሲያሸንፍ በሁለቱ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል፡፡

ኒውካስል ዩናይትድ ከክሪስታል ፓላስ፣ ቶተንሃም ሆትስፐር ከሰንደርላንድ፣ ፉልሃም ከሊቨርፑል እንዲሁም ኤቨርተን ከብሬንትፎርድ በተመሳሳይ ሰዓት ምሽት 12 ሰዓት ላይ ይገናኛሉ፡፡

ትናንት በተደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች አርሰናል ቦርንማውዝን 3 ለ 2፣ አስቶንቪላ ኖቲንግሃም ፎረስትን 3 ለ 1፣ ወልቭስ ዌስትሃም ዩናይትድን 3 ለ 0 እንዲሁም ብራይተን በርንሌይን 2 ለ 0 ማሸነፋቸው ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.