በሁሉም ዘርፍ የምርት ጥራትን ባህል ለማድረግ…
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሁሉም ዘርፍ የምርት ጥራትን እና ተደራሽነትን ባህል ለማድረግ ሁሉም የበኩሉን ሃላፊነት ሊወጣ ይገባል አለ የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት፡፡
የሳኒቴሪ መሃንዲሶችና የቧንቧ ባለሙያዎችን አቅም ለማሳደግ እንዲሁም በቧንቧ እቃዎች ላይ ያሉ ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃዎችን ለማስገንዘብ ያለመ ወርክ ሾፕ በአማን የቧንቧ እቃዎች አዘጋጅነት ተካሂዷል፡፡
የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቴዎድሮስ መብራት በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በሁሉም ዘርፎች የምርት ጥራትን እና ደረጃን ለማስጠበቅ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡
ለታሰበላት አላማ የሚውልና ትክክለኛ ደረጃውን የጠበቀ ብሎም ደንበኞች የሚፈልጉትን ምርትና አገልግሎት ለገበያ ለማቅረብ ሁሉም በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
የምርት ጥራት በአንድ ጀምበር የሚመጣ የአንድ ጊዜ ተግባር አይደለም ያሉት ዋና ሥራ አስፈፃሚው÷ ይሁን እንጂ በሒደትያለማቋረጥ በማሻሻል ባህል ማድረግ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
![]()
የቲ ፍሎው ምርቶች አቅራቢ የሆነው ሞሪንጋ ፋርም ዋና ሥራ አስኪያጅ ሰይፉ ታደሰ በበኩላቸው÷ ወርክ ሾፑ በኢትዮጵያ በግንባታ ዘርፍ ለተሰማሩ አካላት በዘርፉ ያለውን የጥራት ደረጃ በማሳወቅ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አስረድተዋል፡፡
በአማን የቧንቧ እቃዎችም ለምርት ጥራት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅትን የሚጠይቃቸውን መመዘኛዎች የሚያሟሉ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት ለገበያ እያቀረበ ይገኛል ብለዋል፡፡
በዘርፉ ላይ የተሰማሩ ባለድርሻ አካላት እቃዎች ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃን ያሟሉ መሆናቸውን በማረጋገጥ መጠቀም እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል፡፡
አሁን ላይ በኢትዮጵያ ግንባታ እየተስፋፋ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ድርጅታቸው ከውጭ ይገቡ የነበሩ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት የውጭ ምንዛሪን እያዳነ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡
![]()