ማንቼስተር ዩናይትድና ሊድስ ዩናይትድ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ20ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ማንቼስተር ዩናይትድ እና ሊድስ ዩናይትድ አንድ አቻ ተለያይተዋል፡፡
የማንቼሰተር ዩናይትድ ግብ ማቲያስ ኩንሃ ሲያስቆጥር የሊድስ ዩናይትድን ጎል አሮንሰን ከመረብ አሳርፏል፡፡
የሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል በተመሳሳይ ሰዓት ምሽት 12 ሰዓት ላይ ኒውካስል ዩናይትድ ከክሪስታል ፓላስ፣ ቶተንሃም ሆትስፐር ከሰንደርላንድ፣ ፉልሃም ከሊቨርፑል እንዲሁም ኤቨርተን ከብሬንትፎርድ ይገናኛሉ፡፡
የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ ምሽት 2 ሰዓት 30 ላይ ሲካሄድ ማንቼስተር ሲቲ በሜዳው ኢትሃድ ቼልሲን ያስተናግዳል።