የቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ የኢነርጂ ዘርፍ ፕሮጀክቶችን በምርምር ለማገዝ እየሰራሁ ነው አለ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሶማሌ ክልል የተጀመሩ የተፈጥሮ ጋዝና ሌሎች የኢነርጂ ዘርፍ ፕሮጀክቶችን በምርምርና በሰው ኃይል አቅርቦት ለመደገፍ እንቅስቃሴ ጀምሬያለሁ አለ የቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ።
በቅርቡ በሶማሌ ክልል በካሉብ አካባቢ የተፈጥሮ ጋዝን ለሀገር ውስጥ ፍጆታና ለኢንዱስትሪ የሚሆን ፈሳሽ ጋዝ የሚያመነጨው ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍ ተመርቆ ሁለተኛው ምዕራፍ መጀመሩ ይታወቃል።
ከጋዙ ጎን ለጎን በሚገኘው ጥሬ ነዳጅ ላይ ተመሥርቶ የሀገር ውስጥ የነዳጅ ምርት ፍላጎትን የሚቀንሰው የዘይት ማጣሪያ ፋብሪካ ግንባታም ተጀምሯል።
ሜጋ ፕሮጀክቶቹ ካሉበት አካባቢ በቅርብ ርቀት የሚገኘው የቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ ይህንን እድል ወደ ውጤት ለመቀየር እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አሕመድ (ኢ/ር) ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት÷ ተቋሙ ከተፈጥሮ ጋዝ ምርት አንስቶ እስከ ድፍድፍ ነዳጅ የማውጣትና ማጣራት ሂደት ውስጥ ሚና የሚኖራቸውን ባለሙያዎች ለማፍራት የሚያስችሉ ሥራዎችን ጀምሯል።
ለዚህም ዩኒቨርሲቲው በዘርፉ ላይ ትኩረታቸውን ያደረጉ ዘጠኝ የትምህርት ክፍሎችን በመክፈት እስከ ሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት ለመስጠት ወደ ተግባር መግባቱን ተናግረዋል።
ዩኒቨርሲቲው ትልሙን ለማሳካት ልምዱና እውቀቱ ካላቸው 25 የውጭ ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ትስስር መፍጠሩንም አመላክተዋል።
በአንዱዓለም ተስፋዬ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook WMCC
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!