ግብፅ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀለች
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ግብፅ ቤኒንን 3 ለ 1 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅላለች፡፡
የግብፅን የማሸነፊያ ግቦች ሳላህ፣አቴያ እና ኢብራሂም ሲያስቆጥሩ ቤኒንን ከሽንፈት ያልታደገችዋን ብቸኛ ግብ ደግሞ ዶሱ ከመረብ አሳርፏል፡፡
ጨዋታው ቀጥሎ ሲካሄድ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ናይጄሪያ ከሞዛምቢክ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ግብፅ አዘጋጇ ሀገር ሞሮኮን ፣ካሜሩን ፣ሴኔጋል እና ማሊን በመከተል ሩብ ፍጻሜውን የተቀላቀለች አምስተኛዋ ሀገር ሆናለች፡፡