ከንቲባ አዳነች አቤቤ 381 የመኖሪያ ቤቶችን ለአቅመ ደካሞች አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ 381 የመኖሪያ ቤቶችን ለሀገር ባለውለታዎችና አቅመ ደካሞች አስተላልፈዋል።
ከንቲባዋ በንፋስ ስልክ ላፍቶ እና በቂርቆስ ክፍለ ከተሞች በተገነባ ባለ 5 ወለል ህንፃ የሚገኙ ቤቶችን ነው ያስተላለፉት፡፡
የቤት ስጦታ ከተሰጣቸው የሀገር ባለውለታዎች መካከል ታዋቂው ደራሲ ሀብታሙ አለባቸው እና የአብዲሳ አጋ ልጅ ኤልያስ አብዲሳ ይገኙበታል፡፡
ከንቲባ አዳነች በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ አዲስ አበባን ለኑሮ ምቹ ከማድረግ ባለፈ በሁለንተናዊ መልኩ ነዋሪዎቿን ተጠቃሚ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡
በዚህም የከተማዋን ነዋሪዎች የቤት ባለቤት የማድረግ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
በግዛቸው ግርማዬ