Fana: At a Speed of Life!

ሊያም ሮዚኒየር የቼልሲ አሰልጣኝ ለመሆን ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) እንግሊዛዊው አሰልጣኝ ሊያም ሮዚኒየር የምዕራብ ለንደኑን ክለብ ቼልሲ ለማሰልጠን ተሰማምተዋል፡፡

የፈረንሳዩ ክለብ ስትራስቡርግ አሰልጣኝ የነበሩት ሊያም ሮዚኒየር የኢንዞ ማሬስካን ስንብት ተከትሎ ቼልሲን እንደሚረከቡ በስፋት ሲዘገብ ነበር፡፡

የ41 ዓመቱ እንግሊዛዊ አሰልጣኝ ሰማያዊዎቹን ለማሰልጠን ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

አሰልጣኝ ሊያም ሮዚኒየር በሰጡት አስተያየት “የዓለም ሻምፒዮኑን ክለብ ለማሰልጠን ያገኘሁትን እድል ልገፋ አልችልም” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ ሰዓታት ፊርማቸውን በማኖር የምዕራብ ለንደኑን ክለብ በይፋ እንደሚረከቡም ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.