አልጄሪያ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀለች
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አልጄሪያ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን 1 ለ 0 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅላለች፡፡
ምሽት 1 ሰዓት ላይ የተካሄደው ጨዋታ ሙሉ ክፍለ ጊዜ ያለምንም ግብ ተጠናቅቆ ወደ ጭማሪ ደቂቃ አምርተው አልጄሪያ ባለቀ ሰዓት ባስቆጠረችው ብቸኛ ግብ ማሸነፍ ችላለች።
የአልጄሪያን የማሸነፊያ ግብ በ119ኛው ደቂቃ ላይ አዲል ቡልቢና ከመረብ አሳርፏል።
የጥሎ ማለፍ ጨዋታው ቀጥሎ ሲካሄድ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ኮትዲቯር እና ቡርኪና ፋሶ ይገናኛሉ።