ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከቀዳማዊት እመቤት ጋር በመሆን በሼይካ ፋጢማ ቢን መብሩክ የዐይነ ስውራን ትምህርት ቤት ማዕድ አጋሩ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሼይካ ፋጢማ ቢን መብሩክ ዐይነ ስውራን ትምህርት ቤት በመገኘት ማዕድ አጋርተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መረጃ÷ በልደት (ገና) በዓል ቀን ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጋር በመሆን በሼይካ ፋጢማ ቢን መብሩክ የዐይነ ስውራን ትምህርት ቤት በመገኘት መዓድ ተካፍለናል ብለዋል።
ይኽቺን ልዩ ማለዳ በጋራ ማሳለፋችን የገናን እውነተኛ መንፈስ ያሳየንም ሆኗል ሲሉ አመላክተዋል።