Fana: At a Speed of Life!

የገና በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል (ገና) በመላው ኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በዛሬው ዕለት እየተከበረ ነው፡፡

በዓሉ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ በተለያዩ ሐይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች ከመከበሩ ባሻገር÷ ማሕበራዊ ግንኙነትን በማጠናከር፣ ሥጦታዎችን በመለዋወጥ እና የተቸገሩትን በመደገፍ እንደሚበር ይታወቃል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሩሲያ፣ ሰርቢያ፣ ጆርጂያ እና ሌሎች ሀገራት የገና በዓል በዛሬው ዕለት ተከብሮ ይውላል።

የሐይማኖት አባቶች በዓሉን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ምዕመኑ በዓሉን ሲያከብር ስለሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም በመጸለይና በማሰብ እንዲሁም በልዩ ልዩ ምክንያት የምግብ፣ የልብስና የመጠለያ እጥረት ያጋጠማቸውን ወገኖች በመደገፍና በመርዳት ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.