የተለያዩ ሀገራት ኢምባሲዎች እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት ኢምባሲዎች እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል (ገና) የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በኢትዮጵያ የሚገኙ የአሜሪካ እና የእስራኤል ኢምባሲዎች የገና በዓል ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የሰላም እና የደስታ እንዲሆን ተመኝተዋል።
በኢትዮጵያ የካናዳ እና የህንድ ኢምባሲዎችም በተመሳሳይ ለገና በዓል የመልካም ምኞት መዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በኢትዮጵያ የዩናይትድ ኪንግደም ኢምባሲ በበኩሉ÷ የገና በዓል የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታ እና የአንድነት እንዲሆን ተመኝቷል።
በኢትዮጵያ የአርሜኒያ፣ አውስትራሊያ፣ ስዊዘርላንድ፣ ፓኪስታን፣ ኢራን፣ ጀርመን፣ ብሩንዲ እና ጅቡቲ ኤምባሲዎችም በተመሳሳይ ለክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የገና በዓል እንዲሆን ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)፣ የተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ ቢሮ፣ የዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት (አይኦኤም) እና የጃፓን ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ) የገና በዓል የሰላምና የደስታ እንዲሆን የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።