Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ ነዋሪዎቿን የምትንከባከብ ከተማ ሆናለች – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎቿን የምትንከባከብ ከተማ ሆናለች አሉ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

ከንቲባዋ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በጉለሌ ተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ለአቅመ ደካማ ወገኖች ማዕድ አጋርተዋል።

ከንቲባ አዳነች በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ አዲስ አበባ ነዋሪዎቿን የምትንከባከብ ከተማ ሆናለች፤ የተገነቡ የምገባ ማዕከላት ደግሞ ለዚህ ማሳያ ናቸው።

ገና የፍቅር በዓል እንደመሆኑ የማዕድ ማጋራቱም ለነዋሪዎች ያለንን ፍቅር መግለጫ ይሆናል ነው ያሉት።

የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብሩ በ26ቱም የምገባ ማዕከላት መከናወኑን ገልጸው÷ ከሰሞኑ 381 ቤቶች ለአቅመ ደካማ ነዋሪዎች መሰጠቱንም አመላክተዋል።

በጀማል አህመድ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.