Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቱሉ አራራ የተቀናጀ ሞዴል መንደርን በይፋ መረቁ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች ጋር በመሆን የክረምት በጎ አድራጎት መርሐ ግብርን ወደ ላቀ ከፍታ ያሸጋገረውን የቱሉ አራራ የተቀናጀ ሞዴል መንደርን በይፋ መርቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ እንዳሉት÷ ሞዴል መንደሩ በ7 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ነው።

እያንዳንዱ ቤት ሁለት መኝታ ክፍሎችን ጨምሮ በአጠቃላይ አምስት ክፍሎች እንዲኖሩት ተደርጎ ደረጃውን ጠብቆ የተገነባ መሆኑንም ገልጸዋል።

መንደሩ በቤተሰብ ደረጃ ለ150 ዜጎች ምቹና ጽዱ መኖሪያ እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን÷ የመሠረተ ልማት አቅርቦቱም የውስጥ ለውስጥ መንገድ፣ የኤሌክትሪክና የሶላር ኃይል፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ስፍራ እና የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን ያካተተ መሆኑን አብራርተዋል።

የነዋሪዎቹን የኑሮ ደረጃ በዘላቂነት ለማሻሻል መንደሩ የምርትና የገበያ ሰንሰለትን ያካተተ የተቀናጀ አሰራርን ዘርግቷልም ነው ያሉት።

ይህ የልማት ስራ የወተት ላሞች እና የዶሮ እርባታን እንዲሁም የጓሮ አትክልት ልማትን አጣምሮ የያዘ መሆኑን ገልጸው÷ እስከ መገበያያ ስፍራ የሚደርስ የተቀናጀ የንግድ ሰንሰለት እንደተፈጠረለትም አመላክተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.