Fana: At a Speed of Life!

በሁሉም ዘርፍ የምርት ጥራትን ባሕል ለማድረግ…

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሁሉም ዘርፍ የምርት ጥራትን እና ተደራሽነትን ባህል ለማድረግ ሁሉም የበኩሉን ሃላፊነት ሊወጣ ይገባል አለ የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት፡፡

በቧንቧ እቃዎች ላይ ያሉ ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃዎችን ለማስገንዘብ እንዲሁም የሳኒቴሪ መሃንዲሶችና የቧንቧ ባለሙያዎችን አቅም ለማሳደግ ያለመ ወርክ ሾፕ ተካሂዷል፡፡

የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቴዎድሮስ መብራት በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በሁሉም ዘርፎች የምርት ጥራትን እና ደረጃን ለማስጠበቅ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

ለታሰበለት አላማ የሚውልና ትክክለኛ ደረጃውን የጠበቀ ብሎም ደንበኞች የሚፈልጉትን ምርትና አገልግሎት ለገበያ ለማቅረብ ሁሉም በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

የምርት ጥራት በአንድ ጀምበር የሚመጣ የአንድ ጊዜ ተግባር አይደለም ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ÷ ይሁን እንጂ በሒደት ያለማቋረጥ በማሻሻል ባህል ማድረግ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ኢትዮጵያን ወደ ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማድረስ በሁሉም ተቋማት ዘንድ ጥራትንና ተወዳዳሪነትን ቁልፍ ተግባር አድርጎ መያዝ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

አምራች እና አገልግሎት ሰጪዎችን ጨምሮ ሁሉም ድርጅቶች ጥራት እና ዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነት ላይ ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

የቲ ፍሎው ምርቶች አቅራቢ ሞሪንጋ ፋርም ዋና ሥራ አስኪያጅ ሰይፉ ታደሰ በበኩላቸው ÷ መድረኩ በኢትዮጵያ በግንባታ ዘርፍ ለተሰማሩ አካላት በዘርፉ ያለውን የጥራት ደረጃ በማሳወቅ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አስረድተዋል፡፡

ተቋማቸው የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት መመዘኛዎችን በማሟላት እንዲሁም የቧንቧ እቃዎችን በሀገር ውስጥ በመተካት ጥራት ያላቸው ምርቶችን ለገበያ እያቀረበ ይገኛል ብለዋል፡፡

በዘርፉ ላይ የተሰማሩ ባለድርሻ አካላት እቃዎች ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃን ያሟሉ መሆናቸውን በማረጋገጥ መጠቀም እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡

አሁን ላይ በኢትዮጵያ የግንባታ ዘርፉ እየተስፋፋ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ድርጅታቸው ከውጭ ይገቡ የነበሩ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት የውጭ ምንዛሪን እያዳነ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.