መቐለ 70 እንደርታ እና ሸገር ከተማ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ14ኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር መቐለ 70 እንደርታ እና ሸገር ከተማ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።
አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የተካሄደው የመቐለ 70 እንደርታ እና ሸገር ከተማ ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ ውጤት ተጠናቅቋል።
ቀን 9 ሰዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 ማሸነፉ ይታወቃል።
በተመሳሳይ ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም የተካሄደው የድሬዳዋ ከተማ እና የኢትዮ ኤሌክትሪክ ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል።