ሴኔጋል ግብጽን በማሸነፍ ለፍጻሜ አለፈች
አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ሴኔጋል ግብጽን በማሸነፍ ለፍጻሜ አልፋለች።
ምሽት 2 ሰዓት ላይ በተጀመረው ጨዋታ ሴኔጋል ግብጽን 1 ለ 0 ስትረታ ሳዲዮ ማኔ የማሸነፊያ ግቧን ከመረብ አሳርፏል።
ውጤቱን ተከትሎ ለፍጻሜ ያለፈችው ሴኔጋል ከሞሮኮ እና ናይጀሪያ አሸናፊ ጋር በፍጻሜ ጨዋታው ትገናኛለች።
የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታው ቀጥሎ ሲካሄድ ምሽት 5 ሰዓት ላይ የውድድሩ አስተናጋጅ ሀገር ሞሮኮ እና ናይጄሪያ ይገናኛሉ።