Fana: At a Speed of Life!

በኦሬዶ ዶሃ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሬዶ ዶሃ ማራቶን በሁለቱም ፆታዎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል።

በዚህም በወንዶች ማራቶን አትሌት ታምራት ቶላ 2 ሰዓት ከ5 ደቂቃ ከ37 ሰኮንድ በመግባት የቦታውን ሪከርድ በመስበር አሸንፏል።

በውድድሩ ኢትዮጵያዊያኑ አትሌቶች አሰፋ ቦኪ እና ቦኪ ድሪባ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል።

እንዲሁም አትሌት ድንቅዓለም አየለ 4ኛ፣ አትሌት ባለው ይሁንልኝ 5ኛ፣ አትሌት ሙሉጌታ ደባሱ 7ኛ፣ አትሌት ደሳለኝ ግርማ 8ኛ፣ አትሌት ውበት ገ/ህይወት 10ኛ በመሆን ውድድሩን ማጠናቀቅ ችለዋል።

በሴቶቹ ምድብ በተመሳሳይ አትሌት ትዕግስት ገዛኸኝ 2 ሰዓት ከ21 ደቂቃ ከ10 ሰኮንድ በመግባት ቀዳሚ ስትሆን÷ አትሌት ትዕግስት ግርማ እና ጉታ አብዮት ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቅቀዋል።

በዚህም ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ሙሉሀብት ፀጋ 4ኛ፣ ሮማን ግደይ 6ኛ፣ አለምፀሐይ መኩሪያ 8ኛ፣ ሀመልማል ታገል 9ኛ፣ ስንታየሁ 10ኛ በመሆን በውድድሩ የበላይነታቸውን አረጋግጠዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.