Fana: At a Speed of Life!

የሐይማኖት ተቋማት ሰላምና አንድነት ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ምሰሶ ነው – ተስፋዬ ቤልጅጌ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሐይማኖት ተቋማት ሰላምና አንድነት ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ምሰሶ ነው አሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ ቤልጅጌ (ዶ/ር)።

ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በጎፋ እና ባስኬቶ ሀገረ ስብከት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት በእርቀ ሰላም መጠናቀቁን አስመልክቶ በተካሄደ የሰላም ጉባኤ ላይ ነው።

በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ትልቅ አቅም የሚሆኑ ሀገር በቀል የግጭት አፈታት ሥርዓቶች መኖራቸውን አንስተው÷ በክልሉ ችግሮችን በጥበብ በመፍታት ሰላም እንዲሰፍን የተሰራው ተግባር ለሌሎች በተሞክሮነት የሚወሰድ መሆኑን ገልጸዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በበኩላቸው÷ አዲሱ ክልል የሰላም፣ የመቻቻልና የብልፅግና ተምሳሌት እንዲሆን ከሕዝብ ጋር በርካታ ጥረቶች መከናወናቸውን ተናግረዋል።

ለልማትና እድገት ሰላም ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው÷ አሸናፊና ተሸናፊ ሳይኖር ሁሉም እኩል በሰላማዊ መንገድ አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ተሰርቷል ብለዋል።

መለሰ ታደለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.