Fana: At a Speed of Life!

የጥምቀት በዓል መንፈሳዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ ሊከበር ይገባል – ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ‎በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጥምቀት በዓል መንፈሳዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ ሊከበር ይገባል አሉ፡፡

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ መጪውን የጥምቀት በዓል አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት፥ ምዕመኑ ሰላም፣ ፍቅርንና አንድነትን የሚሰብኩ ተግባራትን በማከናወን በዓሉን ሊያከብር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በበዓለ ጥምቀት የተመሠረተውን የጥምቀት ምስጢርና ከጥምቀት የሚገኘውን የልጅነት ጸጋ በማሰብ ማክበር ይገባል ሲሉ አባታዊ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ሰዎችን በሐሳብ የሚለያዩና ከበዓሉ መንፈስ ጋር የሚጋጩ መልዕክቶችንና ምልክቶችን እንዲሁም ዓርማዎችን መጠቀም እንደማይገባም አስገንዝበዋል፡፡

ምዕመኑ በጎ እሴቶችን በጠበቀ መልኩ እንዲያከብር ጥሪ በማቅረብ በዓሉ የሰላምና የበረከት እንዲሆን ቡራኬያቸውን ሰጥተዋል፡፡

በአሸናፊ ሽብሩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.