Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ከ8 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ባለፉት ስድስት ወራት ከ8 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል አለ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ፡፡

የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ህይወት አሰግድ እንዳሉት፥ በክልሉ የሚሰበሰበውን ገቡ ለማሳደግ ለግብር ከፋዩ ማህበረሰብ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን በማዘጋጀት በተከታታይነት ሲሰራ ቆይቷል፡፡

እነዚህ ስራዎች ለገቢው ማደግ አስተዋፅኦ ማድረጋቸውን ገልጸው፥ ክልሉ ካለው ገቢን የማመንጨት አቅም አንፃር አሁንም በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በክልሉ ከተገኘው ገቢ ውስጥ ከ7 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ የሚሆነው ከመደበኛ ገቢ እንዲሁም ከ656 ሚሊየን ብር በላይ ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ የተሰበሰበ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የተገኘው ገቢ የዕዱን 88 ነጥብ 6 በመቶ መሆኑን አንስተው፥ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ80 በመቶ ብልጫ አለው ብለዋል።

የክልሉን ወጪ በገቢ ለመሸፈን በተሰራው ስራም 64 በመቶ በላይ የሚሆነውን መሸፈን መቻሉን አስታውቀዋል።

በቀጣይም ከደረሰኝ አሰጣጥ ጋር ተያይዞ የሚታዩ ጉድለቶችን ለመቅረፍ የአስተምሮና የግብር ህግ ማስከበር ሥራዎች ላይ በተቀናጀ መልኩ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በግማሽ በጀት ዓመቱ የታዩ ክፍተቶችን በመለየት የቀሪ ወራት ዕቅዱን ሙሉ በሙሉ ለማሳካት ይሰራልም ነው ያሉት፡፡

በተራመድ ጥላሁን

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Telegram https://fanamc.com/amharic/

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.