የከተራና የጥምቀት በዓል ምክንያት በማድረግ ለተሽከርካሪዎች የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ
ጥር 10 እና 11 ቀን 2018 ዓ.ም በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የከተራና የጥምቀት በዓል ይከበራል።
በአዲስ አበባም በዋነኝነት በጃን ሜዳ፣ በአቃቂ ቃሊቲ ጥሩነሽ ቤይጂንግ፣ በለሚ ኩራ አራብሳ ሠፈራ እንዲሁም በን/ስ/ላፍቶ ሀጫሉ አደባባይ አካባቢ በሚገኙ ጥምቀተ ባህር ቦታዎች በርካታ ታቦታት ስለሚያድሩና የበዓሉ አክባሪዎች ስለሚወጡ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር፦
👉 ከፈረንሳይ ለጋሲዮን ወደ 6 ኪሎ (ፈረንሳይ ኤምባሲ ድልድይ)
👉 ከቀበና አደባባይ ወደ ምኒልክ ሆስፒታል (ቀበና አደባባይ)
👉 ከጀርመን ኤምባሲ ድልድይ ወደ ምኒልክ ሆስፒታል (ጀርመን ኤምባሲ ድልድይ)
👉 ከኮሪያ ሰፈር ወደ ምኒልክ (ኮሪያ ሰፈር)
👉 ከግንፍሌ ወደ ሳንፎርድ ት/ቤት (ግንፍሌ ድልድይ)
👉 ከቅድስት ማርያም ወደ ጃንሜዳ (ቅድስተ ማርያም)
👉 ከገንዘብ ሚ/ር ወደ 6ኪሎ ቶታል (ገንዘብ ሚኒስቴር)
👉 ከ6 ኪሎ አደባባይ ወደ ፈረንሳይ ለጋሲዮን (6ኪሎ አደባባይ ላይ)
👉 ከቃሊቲ ማሰልጠኛ ጥሩነሽ ቤጂንግ
👉 ከዩኒሳ በዓለም ባንክ ጥሩነሽ ቤጂንግ
👉 ከኮዬ አደባባይ በዋሊያ ጥሩነሽ ቤጂንግ
👉ለሚ ኩራ አራብሳ ሠፈራ አካባቢ
👉 ን/ስ/ላፍቶ ሀጫሉ አደባባይ አካባቢ ከጥር 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 5:30 ጀምሮ በዓሉ እስኪጠናቀቅ ድረስ መንገዶች የሚዘጉ መሆናቸው ተገልጿል።
አሽከርካሪዎችም ታቦታቱ በሚያልፉባቸው ቦታዎች መንገዶች ዝግ መሆናቸውን አውቀው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።
ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙም በነጻ የስልክ መስመሮች 990፣ 991፣ 987፣ 816 እንዲሁም በ011-1-26-43-59፣ 011-5-52-63-02/03፣ 011-5-52-40-77፣ 011-5-54-36-78 እና 011-5-54-36-81 እንዲሁም በእጅ ስልኮች የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን በመጠቀም ጥቆማ መስጠት እንደሚገባም ጥሪ አስተላልፋል።