Fana: At a Speed of Life!

ሞሮኮ እና ሴኔጋል የአፍሪካ ዋንጫን ለማንሳት ይፋለማሉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አስተናጋጇ ሞሮኮ እና ሴኔጋል ዋንጫውን ለማንሳት ወደ ሜዳ ይገባሉ።

ጨዋታው ምሽት 4 ሰዓት ላይ በሞሮኮ መዲና ራባት ፕሪንስ ሙላይ አብደላ ስታዲየም ይካሄዳል።

በደጋፊዎቹ ፊት የሚጫወተው የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን በግማሽ ፍጻሜው ከናይጄሪያ ጋር ያደረገውን ጨዋታ በመለያ ምት አሸንፎ ነው ለፍጻሜ የበቃው።

ሴኔጋል በበኩሏ በግማሽ ፍጻሜው ግብጽን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለፍጻሜ በቅታለች።

ትናንት ምሽት ሶስተኛ ደረጃን ለመያዝ የተደረገው የናይጄሪያ እና የግብጽ ጨዋታ በናይጄሪያ አሸናፊነት መጠናቀቁ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.